Australian and international news and information in Amharic.
Date | Title & Description | Contributors |
---|---|---|
2024-12-18 | በሥነ ግጥም፣ ቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎች ዘርፍ ስመጥር ኢትዮጵያውያን መካከል አንዷ የሆኑት ከበደች ተክለአብ፤ ዳግም ለሕትመት ስላበቁት "የት ነው?" መፅሐፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ። በቀጣዩ ክፍለ ዝግጅታችን አዲስ ስላሳተሙት "ሱታፌ" መፅሐፍ ይዘት ያስረዳሉ፤ ከግጥሞቻቸውም ጥቂቶቹን በአንደበታቸው ያስደምጣሉ። | |
2024-12-17 | Australians lose $32 billion a year to gambling — more per person than any other nation. And it’s affecting diverse communities differently. - አውስትራሊያውያን በዓመት በቁማር 32 ቢሊየን ዶላር ያጣሉ፤ በግለሰብ ደረጃ ከማናቸው አገር በበለጠ። በተለየ ሁኔታም ዝንቅ ማኅበረሰባቱ ላይ ጉዳትን እያስከተለ ነው። | |
2024-12-17 | Learn how to talk about fishing. Plus, find out a bit of history on why Australians love fishing. | |
2024-12-16 | ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ፤ ሜልበርን - አውስትራሊያ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 በሚካሔደው 28ኛው ዓመታዊው የእግር ኳስ ውድድርና የኢትዮጵያ ቀን ክብረ በዓል ላይ ይገኛል። የሕይወት ጉዞውን ከጠዳ እስከ አውስትራሊያ አንስቶ ያወጋል። | |
2024-12-12 |
"በ13ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ብሔረሰቦች መካከል አርጎባ ነበር" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ፤ የ"ኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፍ ደራሲ፤ በኩሽና ኩሻዊነት ዙሪያ ያሉ ብዥታዎችን ያመላክታሉ። የማረቂያ ምክረ ሃሳቦችንም ይቸራሉ። |
|
2024-12-11 |
በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕጋዊ ዕውቅናና ውክልና ያላቸው 76 ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ናቸው ተባለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያውን ደብር ሰየመች |
|
2024-12-10 |
"የጥንቱ የኩሽ ሀገረ መንግሥት ከአሁኑ የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች ጋር ምንም ቀጥተኛ ግንኙነት የለውም" ዶ/ር ግርማ ደመቀ ደራሲ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ ሰሞኑን ለሕትመት ስላበቁት "የኩሽ እና ኩሻዊ፤ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ነገድ" መጽሐፋቸው ጭብጦች ያስረዳሉ። |
|
2024-12-09 |
"ካለፈው ዓመት ዘንድሮ አንድነታችንን አጠንክረናል፤ ኢትዮጵያውያንን አነቃቅተናል" ወ/ት ገነት ማስረሻና አቶ አሕመድ ዳውድ ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና አቶ አሕመድ ዳውድ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ንብረት ኃላፊ ዘንድሮ ከዲሴምበር 25 / ጥር 17 እስከ ዲሴምበር 29 / ጥር 21 ስለሚካሔደው 28ኛው የኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያን ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር መሰናዶና ሂደት ይናገራሉ። |
|
2024-12-09 | አምስቱ የቦብ ማርሌይ ልጆች የሙዚቃ ዝግጅት ኢትዮጵያ ውስጥ በወርኃ ግንቦት ሊካሔድ ነው | |
2024-12-09 |
"ትንሽ ፊደል ቀመስን በሚለውም ውስጥ ኩሽና ኩሻዊነትን በተመለከተ ማደናገር አለ" ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ የሥነ ልሳን ተጠባቢ ናቸው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ታሪክ ዙሪያ የምርምር ግኝቶችን ያካተቱ ደርዘን የተጠጉ መፅሐፍትን ለሕትመት አብቅተዋል። ሰሞኑንም በኩሽ ዙሪያ በውዥንብር የታጨቁ ዕይታዎችን ለማጥራት በሚል ሙያዊ ኃላፊነት ዕሳቤ "ኩሽ እና ኩሻዊ" በሚል ርዕስ ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ የፈጀ ጥናታዊ ሥራቸው የተካተተበትና የሁለት ዓመታት የጽሕፈት ጊዜያትን የወሰደባቸ... |